የጎንደር አካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ2017 በጀት ዓመት ለማዕከሉ አገልግሎት የሚዉሉ የስልጠና ጥሬ እቃዎች ፣የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች ፣የጽዳት እቃዎች ፣የአይሲቲ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣የልብስ ስፌት መኪና ማኩክ ፣የ3L መኪና ጎማ ፣የ3L-166 ኮድ 4-01171 ለሆነ መኪና የኪሎ ሜትር ጌጅ ሙሉዉን ፣የህንፃ መሳሪያ እቃዎች እና በማዕከሉ ጊቢ ዉስጥ ለሚሰለጥኑ አካል ጉዳተኞች ምግብ አብስሎ ለመመገብ በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተለዉን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸዉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ እና የግብር ክፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪ ዋስትና የዋጋዉ አንድ በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ማዘዣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በዋና/ገ/ያዥ ቢሮ. ቁ 10 የማይመለስ00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ የሚለየዉ በሎት ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በማዘጋጀት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- የጨረታዉ ማስታወቂያ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆይና የመክፈቻ ቀን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የጨረታዉ ሳጥኑ ታሽጎ በዚህ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በማዕከሉ ግዥ/ፋ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የመንግስት የሥራ ቀናት በተጠቀሰዉ ቀንና ስዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ሰዉ ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይልም ፣የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጣ ተቀባይነት የለዉም የዕቃዎቹ የግዥ መጠናቸዉ000 ብር በታች ከሆነ ያለ ቫት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በማዕከሉ በግንባር በመቅረብ ወይም በስ.ቁ 058 211 72 33 /09 89 52 56 06 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ሙሉ መግለጫዉን እና መመሪያዉን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አድራሻችን ጎንደር ከተማ ቂርቆስ ቀበሌ 06 አሽዋ ሜዳ ት/ቤት/ጎን ነዉ፡፡
- አሸናፊዉ ዉል የሚወስደዉ ጨረታዉን ያሸነፈበት በደብዳቤ ሲገለፅ ነዉ፡፡
- ማሳሰቢያ ፡- መ/ቤቱ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
የጎንደር አካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል