በአፈ/ከሣሽ ነገሰ ጤናው እና በአፈ/ተከሣሽ ምስጋናው አላምራው መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በደ/ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 09 የሚገኝ በምሥራቅ አንተነህ አዛዥ፣ በምዕራብ ይመኙሻል በላይ፣ በሰሜን መንገድ እና በደቡብ ክብሬ እሱባለው የሚያዋስነው 200 ካ.ሜ ቦታ ካርታ ቁጥር K/0508 የተመዘገበ በጨረታ መነሻ ዋጋ 529,750.12 /አምስት መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር ከአስራ ሁለት ሳንቲም/ በሐራጅ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡ በመሆኑም ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ በዕለቱና በሰዓቱ በመገኝት የመነሻ ዋጋውን ¼ ኛውን እና መታወቂያ በመያዝ ቀርቦ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡