ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
102

የደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በዘርፍ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በደረሰኝ በመክፈል ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ስለትክክለኛነቱ በማህተም በማረጋገጥ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማየት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደምበጫ ከተማ /ገ/ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ/ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ይሆናል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ዋጋውን በመሙላት፣ የጨረታ ሠነዱን ገልፆ በመፃፍ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ፣ የቫት ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎችን በአንድ ፖስታ በማድረግ በፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም፣ ስም፣ ፊርማ፣ አድራሻ በማስቀመጥ ለደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  11. በተራ ቁጥር 10 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  12. 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሠነዱ ላይ ከተገለፀው የዕቃ ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ውጪ ሌላ መጥቀስ አይቻልም፡፡
  14. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ደምበጫ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
  15. የግዥ አቅርቦቱን አሸናፊው ውል በያዘ አስር ቀናት  ውስጥ ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት በማጓጓዝ እና በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ደምበጫ ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  16. መ/ቤቱ አሸናፊውን በሎት በጥቅል ዋጋ በማወዳደር አሸናፊውን የሚለይ ይሆናል፡፡
  17. ግብርና ታክስ የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  18. ቅድሚያ ክፍያ ጽ/ቤቱ የማይከፍል መሆኑ ይታወቅ፡፡
  19. ተጫራጮች የጨረታ ሰነዱን ሙሉ በሙሉ የመሙላት ግዴታ አለባቸው፡፡
  20. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር0587730281/0920514020/0912928346/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

ደምበጫ ከተማ ገንዘብ /ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here