ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
93

በአበክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የአማራ ህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማከፋፈያ ማዕከል በ2017 በጀት ዓመት  ለተለያዩ ክፍሎች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ሎት 3  የኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ሎት 4 የቢሮ ዕቃዎች ፣ሎት 5 የጥገና እቃዎች እና ሎት 6 የተሽከርካሪ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፋ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች 1 ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ውድድሩ በሎት ስለሆነ ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት አለባቸዉ፡፡
  6. ስለ ጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ /ስፔክ/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ከፍሎ በመዉሰድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሥራ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በማዕከሉ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅጽ መሰረት የነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በመሙላትና በየገጹ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማ እና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን  ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15  ቀናት 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በዚሁ እለት 11፡30 ይታሸጋል፡፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ቢሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው ባይገኙም ማዕከሉ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
  11. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 04 15 /058 320 19 92 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058 320 30 88 መጠየቅና ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡ ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጎን

የአማራ ህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማከፋፈያ ማዕከል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here