ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
93

በአዊ ብሄረሰብ  ዞን የአዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ሎት 1 የጽ/መሳሪያ እና ቋሚ አላቂ ዕቃ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 3  የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ሎካል ፈርኒቸር ፣ሎት 4 የቤትና የቢሮ ዕቃዋች ኢምፖርትድ  ፈርኒቸር  ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እንዲሁም ሎት 6 የቅየሳ መሳሪያ (ቶታል ስቴሽን) እና ጀነሬተር  በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ እያንዳንዱን ሎት  በተናጠል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን  መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የግዥው /የአገልግሎቱ/ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እያንዳንዱን ሎት በማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል አዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / ወይም የዕቃውን /አገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ  በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ አዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ህጋዊ ደረሰኝ መሂ 1 ተቆርጦ ኮፒውን  ከሠነዱ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 16ኛው  ቀን 4፡00 ድረስ  በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. እንደ በጀቱ አቅም ሃያ በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. በእያንዳንዱ ምድብ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት መስፈርቱን በማሟላት ከእያንዳንዱ በተናጠል ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ በ16ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ሠዓት ይከፈታል፡
  13. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 ሥራ ቀናት በኃላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በአዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት በማስያዝ ውሉን መፈጸም ይኖርበታል፡፡ በተባለው ቀን መጥቶ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  14. አሸናፊው ውል ከፈጸመ በኃላ የአሸነፋቸውን  ዕቃዎች  አዲስ ቅዳም ከተማ  ድረስ  አጓጉዞ ያደርሳል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ሰለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 450 06 59 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገን//ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here