የግዥ መለያ ቁጥር አ/ማ/03/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ኮሚሽን በጦርነቱ ለተጎዱ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች ማለትም ሎት 1 ጠረጴዛ እና ወንበር እንዲሁም ሎት 2 ደስክ ቶፕ ኮምፒዉተር እና ፕሪንተር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እቃዎች የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክተሬት ቢሮ ቁጥር 007 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በ16ኛዉ ቀን እስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ግምገማ ለሚያስፈልጋቸዉ ዕቃዎች የመጫረቻ ሰነዱን በትክክል ከሞሉ በኋላ ቴክኒካሉን እና ፋይናሻሉን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን እና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 222 05 80 በመላክ እንዲሁም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44 /058 220 96 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ኮሚሽን