የባህርዳር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017ዓ.ም በጀት አመት ለመደበኛ ሰልጣኞች ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ሎት1.የህንጻ ግንባታ ማሰልጠኛ፣ ሎት2. የኤሌክትሪሲቲ ማሰልጠኛ ፣.ሎት3. የኤሌክትሮኒክስ ማሰልጠኛ ፣ ሎት4. የውሃ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስሆነም የሚከተሉትን መስፈርቾች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- ጨረታው ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የማይመለ ስከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ሲሞሉ በፖስተው ላይም ሆነ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታውን በሚሞሉበት ጊዜ በጨረታ ዋጋው ማቅረቢያ ላይ ምንም አይነት በነጠላም ሆነ በጥቅል ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ጨረታው በሚሞላበት ጊዜ በተጠየቀው መለኪያ መሰረት መሙላት ይኖርባችኃል፡፡
- እያንዳንዳቸውን የእቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 17 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ3ወር የሚቆይ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወደደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ብር አንድ በመቶ በኮሌጁ ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ /ማስያዝ በጥቃቅን የሚወዳደሩ ከሆነ ከኢንተርፕራይዝ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው እለት 4፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ ጨረታውን በጥቅልም ሆነ በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኮሌጁ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ በሙሉ ሆነ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ያሸነፈው ድርጅት ንብረቱን ከኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ በሙያተኛ በማረጋገጥ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ የስልክ ቁጥር እና ፋክስ ቁጥር 058 218 0574 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
ባህር ዳር ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ