ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
147

ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ2016 በጀት ዓመት ለሚገነባው የከሚሴ እናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት የሳኒቴሪ  እና ኤሌትሪክ ዕቃዎችን ለመግዛት እና የኢንስታሌሽን ሥራ ለማሰራት ስለሚፈልግ ዕቃዎችን ለማቅረብና የኢንስታሌሽን ሥራ ለመሥራት ለሚፈልጉ ተቋራጮች በዘርፉ የተስማሩ ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡  በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢዎችና ባለሙያዎች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡ ሎት 01 የሳኒታሪ ኢንስታሌሽን  የእጅ ዋጋ ሥራ፤ /ደረጃ 8 እና በላይ የሆኑ በሳኒታሪ ኢንስታሌሽን/፣ ሎት 02 የውሃ ስርገት መከላከያ /Water proofing/ ሥራ ዕቃዎችን በማቅረብ መሠራት /ደረጃ 8 እና በላይ የሆኑ በሳኒታሪ ኢንስታሌሽን ሥራ ወይም በውሃ ስርገት መከላከል ስራ፣ ሎት 03 የኤሌትሪክ ኢንስታሌሽን  የእጅ ዋጋ ሥራ ደረጃ 8 እና በላይ የሆኑ በኤሌትሪክ ኢንስታሌሽን፣ ሎት 04 የሳኒታሪ ዕቃ አቅርቦት እና ሎት 05 የኤሌትሪክ ዕቃ አቅርቦት፡-

  1. ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፡፡ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከዋናው ጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ እና የጨረታ ሰነዱን ኮፒ ለብቻ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የባንክ ጋራንቲ /ኦሪጂናል /ዋና/ ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢሹራንስ ማቅረብ አይቻልም /የተከለከል ነው፡፡ ተቀባይነት የለውም፡፡
  3. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን የጨረታ ማስከበሪያ በማቅረብ ምትክ ተቋማቱን ከአደራጀው ከአነስተኛና ጥቃቅን ጽ/ቤት በሃላፊው በሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአካባቢ ማስታወቂያ እና በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10/አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000226904852 ወይም በአባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 2042111083440043 ገቢ በማድረግ ሰነዱን ወልድያ ከተማ ጎማጣ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ላይ ይታሸጋል፤ በሚቀጥለው ቀን ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይታገድም፡፡
  6. ክፍያን በተመለከት የሳኒቴሪ ዕቃ አቅራቢው ከሚሴ ፕሮጀክቱ ጽ/ቤት ድረስ አቅርበው የዕቃው ትክክለኛነት በባለሙያዎች ሲረጋገጥ የሚከፈል ይሆናል፤ የገጠማ ሥራ የሚያከናውኑ ባለሙያዎች በተሰራ ስራ ልኬታ መሰረት በባለሙያ ሲረጋገጥ በአቅራቢዎች በንግድ ባንክ /አባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥራችው ገቢ ይሆናል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ ጨምሮ መሙላት አለበት፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
  9. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-14716182 /09 12918214 /0912014010 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here