ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
73

የዋድላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለዋድላ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የመንገድ ሥራ ማሽነሪ ኪራይ ማለትም /ዶዘር ፣ሮሎ ፣ኤክስካቫተር ፣ግሬደር ፣ሻወር ትራክ ፣ሲኖ ትራክ /ኪራይ ፣ሎት 2 የመኪና ጎማ ፣ሎት 3 ጽ/መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች /ድርጅቶች/ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶች ማሟላት  ይኖርባችኋል፡፡ የመንገድ ማሽነሪ ጨረታው የሚከናወነው በእያንዳንዱ ማሽነሪ በተናጠል ይሆናል፡፡

  1. ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ አቅራቢዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ስፔስፊኬሽን እና መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች የተዘጋጀውን እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በአዲሱ የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይኖርባችኋል፡፡
  6. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  7. ይህ ግልጽ ጨረታ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት 9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትንና ዋጋ የሞሉበትን ሙሉ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን በሚገዙበት ወቅት ናሙና መያዝ ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጽ/ቤቱ ያቀረበውን ናሙና በማየት ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ሁለት በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ ባሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በመመሪያው መሰረት ማስያዝና ወረዳው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታውን በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  12. ስለጨረታው ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 09 20 01 39 41 /09 12 89 76 71 /09 35 21 60 96
    ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here