የባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የወረዳው ሴ/መ/ቤቶች የቢሮ ግንባታ ዲዛይን G+3, G+2 እና G+0 ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ህንጻዎችን ዲዛይን ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በህንፃ ስራ አማካሪነት ወይም የመሀንዲሶች ቢሮ አማካሪነት ደረጃ 3 እና ከዚህ በላይ የሆነ፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘርፍ አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የቫት ተመዝጋቢና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸው ባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ወይም ስልክ ቁጥር 0582270647 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶችን የጨረታ ማስከበሪ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2በመቶ በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀናት ይሸጋገራል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ከባንጃ ገንዘብ ጽ/ቤት በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት በ22ኛው ቀን በ3፡30 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ባንጃ ገንዘብ ጽ/ቤት ፍላጎት ያለው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኘበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሉ በጨረታ መክፈቻ እለት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን ለመክፈት የሚያግደው የለም፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ በመመሪያው መሰረት የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አሽገው ከሚያስገቡት ሰነድና ፖስታ ላይ አድራሻ እና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀናት ነው፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በቴክኒካልና በጠቅላላ ዋጋ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
የባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት