በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአምባጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያ እስቴሽነሪ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 4 የመኪና እቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡ የመወዳደሪያ መስፈርቶቹም፦
- በየዘርፍ የዘመኑን የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና ናሙና የሚያስፈልጋቸው ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ዘወትር በሥራ ስዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በተናጠል በየሎት ምድባቸው የሚለይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፋያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታ 1ኛ የወጣውን ውል እስከሚወስዱ ድረስ 2ኛ የወጣው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአምባጎርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሥዓት ማስታወቂያው ጋዜጣ ከወጣበት 26/05/2017 ዓ.ም እስከ 10/06/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታውን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 11/06/2017 ዓም በተዘጋጀው ሳጥን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ብሔራዊ በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን
ይሆናል፡፡ - መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከአምባጎርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 118 08 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአምባጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት