የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ቡድን ለቢቡኝ ወረዳ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት በገና መምቻ ቀበሌ አረፋ ወንዝ የካናል ጥገና እና ማራዘም ሥራ በ2017 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ ለመጫረት የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኃል፡፡
- በአዲሱ አዋጅ መሠረት የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬትና በመስኖ አውታር ሥራ የሰራና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችል፡፡
- በውሀ ሥራ ኮንስትራከሽን (WWC) ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሙያ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻዉ በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የአሰሪዉ መሥሪያ ቤትና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የጨረታ አሸናፊዉ የዉል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋውን አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ/ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- የመስኖ ካናል ጥገና እና ማራዘም የሥራ ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን00 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ00 /ሀያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸዉን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግዥ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ከ26/05/2017 እስከ 16/06/2017 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሉቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ/ን/አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በ22 ኛዉ ቀን በ17/06/2017 ዓ.ም 3፡00 ይታሸጋል በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ሃያ በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም በአጠቃላይ በ2014 በጀት ዓመት የወጣውን የተሻሻለውን የግንባታ የግዥ መመሪያ ተግባራዊ የምናደርግ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 00 47 /49 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት