የአዴት ሆስፒታል የግ/ዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ ሂደት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 4 ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንጋብዛለን፡፡
- በዘመኑ የታርስ የንግድ ፈፈድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙት የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሰፊኬሽን)ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ እስከ ዜሮ ነጥብ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአዴት ሆስፒታል በግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 03/06/2017 ዓ.ም እስከ 17/06/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በቀን 18/06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ከጨረታው ሃያ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሽናፊው ድርጅት የሚመረጠው በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ (ሎት) የሞላው ነው፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዥ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ቢሮ ቁጥር 08 በአካል ቀርበው ማናገር ይቻላል፡፡
የአዴት ሆስፒታል