የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ንብረት ለሆኑት የተለያዩ ከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማ ከነ ካላማዳሪዉና ከነፍላፑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ያላቸው፡፡
- በስሙ የታተመ ማህተምና ደረሰኝ ያላቸዉ፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 200,000,00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 03/06/2017 ዓ.ም እስከ 18/06/2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በዚሁ ቀን በ18/06/2017 ዓ.ም ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታዉን ለመክፈት እንገደዳለን፡፡
- አሽናፊዉ የሚለየዉ በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበ ይሆናል፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማጓጓዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብረት አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 18 78 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን