በምሥራቅ ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ፍ/ቤት እና የመርገጭ ንውስ ወረዳ ፍ/ቤት የግፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚዉል ሎት 1 ጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 3 ህንፃ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈልጉ ማንኛዉም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈረቶች ማሟላት ይኖረባችዋል፡፡
- ዘርፍ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር ካለዉ ፓስታ ከዉጭ አያይዞ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርተቶች የሚያሟሉ ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ስዓት ሸበል በረንታ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 የዕድዉኃ ከተማ ድረስ በመቅረብ ማስገባት የሚችሉ፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፈት ሆኖ በ16ኛዉ ቀን በ3፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚህ ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል /ዝግ/ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማቸዉንና ማህተማቸውን በማድረግና በፓስታ በማሸግ ሰነዱን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በሸ/በ/ወ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በተጠቀሰዉ ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሁሉም የተበተኑት ሰነዶች 15 ቀን ሳይሞላዉ ሰነዱ ከተሰበሰበ ቀኑ እስኪሞላ መጠበቅ ሳያስፈልግ በግዥ መመሪያዉ መሰረት ሰነዱ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ሳይገኙ ቢቀሩ ጨረታዉን ከመክፈት የማያስቀረዉ መሆኑንና በጨረታዉ ሂደት ለሚወስኑ ዉሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ በአሸነፈበት ዋጋ ሸበል በረንታ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ የአሸነፉቸዉን ዕቃዎች በአይነትና በመጠን ቆጥሮ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
- ዋጋ ሊሞሉ እያንዳንዱ ሰነድ መሞላት አለበት፡፡ ሥርዝ ድልዝ ካለበት ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸዉ፡፡ የጨረታ ሰነዱንም በሎት /ዋጋዉ/ የሚካሄደዉ ስለሆነ የተዘረዘሩትን እቃዎች በጠቅላላ ያልሞላ ከጨረታ ዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ ዉል ሲይዝ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የዉል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 247 00 16 ደውለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሸበል በረንታ ወረዳ ፍ/ቤት