ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
110

 ቁጥር ግጨ 04/2017

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና እና የህትመት አገልግሎት ለ1/አንድ/ ዓመት የሚቆይ አመታዊ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል፤ የእቃው ግዥ መጠን በኢትዮጵያ ብር ከ200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ ቢሮ ቁጥር 101 ወይም 102 በአካል በመቅረብ የማይመለስ የኢትዩጵያ ብር 150 (አንድ መቶ አምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ  ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፓስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህር ዳር ከተማ በሚገኘው በአብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ላይ ይከፈታል፡፡
  4. በመሆኑም በዕለቱ ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም         በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን በ16ኛወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ   በሚቀጥለው የስራ  ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት 1,000 /አንድ ሽህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፓስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚገዙ እቃዎች /አገልግሎቶች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን) ፤መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን  ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ፡- አብክመ ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582201356 /0582200839 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here