የደብረ ማርቆስ ደም ባንክ አገልግሎት ለጽ/ቤቱ አገልገሎት የሚውሉ ብስኩት፣ የታሸገ ውሃ የጽዳት እቃዎች፣ ህትመትና ፕላስቲክ ወንበር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመገዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግደ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመስከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤቱ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ 03/06/2017 ዓ.ም አስከ 17/06/2017 ዓ.ም ከ2፡30 አስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በደብረ ማርቆስ ደም ባንክ የግ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በቀን 18/06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የጨረታውን ሃይ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ካለም ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የእቃውን ርክክብ በተመለከተ አሸናፊዉ ድርጅት ደብረ ማርቆስ ደም ባንክ አገልግሎት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የግዥው መጠን /ቫት/ የሚገባ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎችንና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉትን ብቻ የሚጋብዝ ይሆናል፡፡
- ውድድሩ በድምር ወይም በሎት መሆኑን እንገልፃስን፡፡ በከፊል የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር ላይ ዋጋ መሙላት ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወደም በስልክ ቁጥር 058 771 10 50 በመደወለ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ማርቆስ ደም ባንክ አገልግሎት