ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

አዊ ብሔረሰብ አስ/ዞን የቻግኒ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 የዉሃ እቃ፣ ሎት 5 የኤሌክትሪክ እቃ፣ ሎት 6 የደንብ ልብስ፣ ሎት 7 የመኪና ጎማ፣ ሎት 8 የልብስ ስፌት መኪና እና ሎት 9 ህትመት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለቸው፡፡
  2. የግብር ከፈይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200.000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከተቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቸቻው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የእቃው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ቻ/መ/ደ/ሆስፒታል የእለት ገቢ ስብሳቢ ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና ለሚወደደሩበት እቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ ከተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከሆስፒታላችን ግቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በፖስታ በማሽግ ማሰያዝ አለበችሁ፡፡ ነገር ግን የጨረታ ማሰከበሪያ በቼክ ካሰያዙ ከውድድር ውጭ ያደረጋል፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ሰነዱን በመሙላት ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር በአንድ ኦርጅናል ፖስታ በማሽግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ግ/ፋ/ን/አስ/ዳ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 ውስጥ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማሰገባት ይኖርባችኋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቻ/መ/ደ/ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን 3፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሰይ ሰዓት ተሸጎ በተመሳሰይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም አድርጎ መመለስ አለበት፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፈበትን እቃዎች ቻ/መ/ደ/ሆስፒታል ንብረት ክፍል ቢሮ ቁጥር 52 ድረስ በማምጣት የማሰረከብ ግዴታ አለበቸው፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቁ ነው፡፡
  13. ሰለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 556 20 09 ወይም ቻ/መ/ደ/ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 ድረስ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይቻላል፡፡
  14. ውድድሩ በሎት (ጥቅል) ድምር መሆኑን አውቀው የተጠየቁትን እቃዎችን ሙሉ በሙሉ እንዲሞሉልን እንጠይቃለን፡፡

የቻግኒ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here