የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 5 የአገር ውስጥ ፈርኒቸር እና ሎት 6 የውጭ ፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 5 የአገር ውስጥ ፈርኒቸር እና ሎት 6 የውጭ ፈርኒቸር እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዞኑ አድራሻ ምዕራብ ጎንደር ዞን ገ/ውሃ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቢሮ ሶስተኛ ፎቅ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደርሰኝ መሂ1 በተቆጠረ በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የጠቅላላ ግዥውን ዋጋ ሁለት በመቶ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ግዥን ዋጋ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ ማስገባት ወይም በተጫራቾች የሚሞላውን የጨረታ ማስረከቢያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱን ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታውን ለመገምገም በርካታ ጊዜ ለማይወስዱና ውስብስብ ላልሆኑ ግዥች ከአረባ (40) ቀናት መብለጥ እንደሌለበት እያወቁ የመጫረቻ ሰነዱን መሙላት አለብዎት፡፡
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኃላ በተጨማሪ ውል እስኪቋረጥ ድረስ ለሚቆይ ሃያ(20) ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ግዥና ፋይናስ ቡድን መሪ ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ዘወተወር በሥራ ሰዓት 03/06/2017 ዓ.ም እስከ የካቲት 17/06/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቹሃል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ15 ቀን በጋዜጣ ተለጥፎ ቆይቶ በ18/06/2017 ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ምዕ/ጎ/ዞ/ ፖሊስ መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ግቢ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ድምር ስለሆነ የሙሉ እቃ ዋጋ መሙላት አለበት ካልተሟላ ግን ከጨረታ ወጭ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ ዋጋ እና የሞዴል መረጃን እንዲሁም የማይነበብ ሥርዝ ድልዝ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 331 05 94 /09 18 23 70 63 /09 18 58 10 34 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ግዥ ፈፃሚ አካል የጨረታውን አሸናፊ በሚመርጥበት ጊዜ መለኪያው ተለይቶ የሚታወቅ እስከሆነ ድረስ በእያንዳንዱ የእቃ መለኪያ የተሰጠውን የነጠላ ዋጋ ወይም ሌሎች የውል ቃሎችና ሁኔታዎችን ሳይለወጡ የዕቃውን ብዛት ወይም መጠን እሰከ ሃያ በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት ወይም /ሲፒኦ/ በማስያዝ በምዕ/ጎ/ዞ/ዐቃቢ ህግ መምሪያ በመቅረብ ውል መውሰድ የሚችሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም የምክንያቶቹን አግባብነት እንዲያስረዳ አይገደድም፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ