ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
110

ቁጥር 05/2017

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን /አሚኮ/ የዋናዉን ቢሮ ሎት 1 የግራዉንድ ፍሎወር ኢንቴረር ዲዛይንና የኢንቴረር ሥራ እንዲሁም ሎት 2 የአሚኮ የዋናዉ ቢሮ አራተኛ ፎቅ ኢንቴረር ዲዛይንና የኢንቴረር ሥራ ለማሰራት ደረጃ 5 እና በላይ የሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ እና ህንፃ ሥራ ተቋራጭ ከነሙሉ ዕቃዉ የዕጅ ዋጋ ጨምሮ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 /ሃያ አንድ/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ  1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመግዛት  አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104  መዉሰድ  ይቻላል፡፡ ሰነዱን የቴክኒክ እና የፋይናስ ሰነዶችን ለየብቻ በመሙላት ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ  በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡ በቴክኒክ ምዘና 70 እና በላይ ነጥብ  ያመጡ ድርጅቶች ወደ ፋይናንስ ዉድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው በ22ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ስፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት 22ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚፈለጉት የኢንቴረር ዲዛይን እና ሥራዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፊኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here