ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
119

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ዋና ጽ/ቤት ለፎገራ ወረዳ  ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ማለትም ሎት 1 ኤክስካቫተር ከነነዳጁ ኪራይ፣  ሎት 2 ቀያማ አፈር ገረገንቲ እና ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃ መግዛትና መከራየት ይፈልጋል፡፡  የተገለጹትን  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ መወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለምዝገባ በሚመጡበት ወቅት

  1. በዘመኑ የታደሠ በዘርፋ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታ መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴትታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት ፎ/ወ/ገ/ኢ/ል/ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ አምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላትና በደንብ ፖስታውን በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር በማድረግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጽ/ቤታችን ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ለሎት 1 ብር 140,000 /አንድ መቶ አርባ ሽህ ብር/ ለሎት 2  ብር 20,000 /ሀያ ሽህ ብር/ ለሎት 3 ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ጨረታ 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  6. አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  7. ሰነዱን ለሚገዙ ተጫራቾች ዝርዝርና ስፔስፊኬሽን ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ድርጅት ውል እንደያዘ ጨረታ ላላሸነፋት አካላት ተመላሽ ይሆናል፡፡
  9. አንድ ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተተንርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  10. አሸናፊው በውሉ መሠረት ከአላስረከበ መ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን መረዳት ይኖርበታል፡፡
  11. በጥቃቅንና አንስተኛ ተደረጅተው ለሚመጡ አካላት ካደራጃቸው ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  13. ኤክስካቫተሩ የፈረስ ጉልበቱ 320 HP የሆነ የአካፋ መጠን 1.5 ሜ/ኩ መሸከም የሚችል ማሽን ለ672 ሰዓት የሥራ ቦታው ጉማራ ወንዝ ርብ ወንዝና ጓንታ ወንዝ ሲሆን ገረገንቲው የሚቀርበው ርብና ጉማራ ነው፡፡
  14. መሥሪያ ቤቱ ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል ከመፈራራሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው መጠን ላይ መጨመረ ወይም መቀነስ አሰፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአሸናፊ ተጫራች የቀረበው በወድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ ሃያ በመቶ መቀነስ ወይም መጨመር የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 446 20 26 በመደወል ጠይቀው መረዳት ይችላሉ፡፡
  16. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፎገራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here