የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ድርጅት በሀገር ውስጥ ገበያ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የ2016 በጀት ዓመት ሂሳብ ለማስመርመር (ኦዲት) ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
- ኦዲትን በተመለከተ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መሥሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ተቋሞቹ ለመስጠት እውቅና ካላቸው)፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፣ ሕጋዊ ሥራ ፈቃድ፣ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት /ቲን/ ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ ሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ መሥሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው በተገለጸው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን እቃ ወይም አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላት፤ የቴክኒክ ማወዳደሪያ ለሚጠይቁ ደግሞ “የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ”፤ የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርፕራይዙ ዋና መሥሪያ ቤት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይዘጋል፤ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሸጋገራል፤ ተጫራቾች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፤ ስርዝ ድልዝ ካለው አንድ ጊዜ ብቻ አግድም መስመር በማድረግና ፓራፍ ካልተደረገበት ተቀባነት አይኖረውም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15 /09 83 58 36 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡