ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
103

የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብ /አ/ቡድን መሪ በበጀት ዓመቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 የእህል አቅርቦት፣ ሎት 2 የወጥ ማጣፈጫ፣ ሎት 3 አትክልትና ፍራፍሬ፣ ሎት 4 የማገዶ እንጨት፣ ሎት 5 ዘይትና ፊኖ፣ ሎት 6 እስቴሽነሪ፣ ሎት 7 የግንባታ ዕቃዎች፣ ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 9 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ከሎት 1 እስከ ሎት 5 ያሉትን ለ6 ወር ውል ወስዶ ከተቋሙ ድረስ የሚያቀርቡ ሲሆን ከሎት 6 እስከ ሎት 9 ደግሞ በወቅቱ ገዝቶ መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችሉትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን ከዚህ በታች ያሉ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የሚያቀርቡ፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ለግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ የሚሞሉትን አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፕኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የአሸነፈውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈውን እቃ ጭልጋ ማረሚያ ቤት መጋዝን ድረስ የሚያቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጅዎች ማለትም ዋናውንና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ ቡድን መሪ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ ቀናት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከየካቲት 10 ቀን 2017 እስከ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርበቸዋል፡፡ የጨረታው ሳጥን የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቡድን መሪ ቢሮ የካቲት 25 ቀን 2017 ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 00 09 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ:-

  1. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
  2. በሎት የተዘረዘሩት እቃዎች በጥቅል ዋጋቸው አሸናፊው ይለያል፡፡
  3. በሎት የተዘረዘሩት ናሙና ማቅረብ ያስፈልጋል ፡፡

የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here