ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
89

በደ/ጎንደር ዞን አ/ዘመን ከተማ የሚገኘው ርብ ኃላ/የተወሠነ የኅብረት ስራ ማኅበራት ገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን ቀበሌ 04 በመደበኛ በጀት ለጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ባለቢዝመንት ሦስተኛ ፎቅ (B+G+3 ፎቅ) ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለሚቀርቡ ለብረት አቅራቢዎች በወስን ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ በመሆኑን  ይጋብዛል፡፡

  1. አቅራቢዎች ህጋዊና በዘመኑ የታደሠ የንግድ /የስራ/ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የወጣው ጨረታ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ እንደሚሆን ሲገመት የተጨማሪም የእሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀረቡት የመጫረቻ ሰነድ በአማረኛ ቋንቋ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በሚሞሉበት የመወዳደሪያ ሃሳብ  ስማቸውን፤ ፊርማቸው እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖረባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በአ/ዘመን ከተማ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት የመጫረቻ ሠነዱን ዋናው ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በአካል /ህጋዊ ወኪላቸው በኩል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ መዝጊያው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  8. የብረት አይነት፤ ብዛትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. የመጫረቻ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን 15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. የመጫረቻ ሰነዱ በ16 ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ማስገባትና በ4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች/ በተገኙበት/ ባይገኙም/ ይከፈታል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ሰነዱ በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦሪጅናል ሰነዱ ፖስታ ውሥጥ በማድረግ  መቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ዩኒዬኑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. የብረት አቀራረብ ሁኔታ በተመለከተ ተጫራቾች መመሪያ ይመልከቱ፡፡
  14. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
  15. ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዬችን በስልክ ቁጥር 058 444 00 61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ርብ ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ስራ ማኅበራት ገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here