በምሥራቅ ጐጃም ዞን የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል ለአገልግሎት የሚውል ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፎቶ ኮፒ ማሽን፣ የህክምና ሲቢሲ ማሽን እና ፕሪንተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች እቃዎችን ወይም አገልግሎቾችን ለማቅረብ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ ዓመት የሞላው ከሆነ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግሥት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መሥሪያ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 00 (ሃምሳ ብር) ለገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡0ዐ ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግ ጨረታውን ላወጣው መሥሪያ ቤት በጽሑፍ ወይም በፋክስ ቁጥር ዐ58 661 ዐ2 64 ወይም በስልክ ቁጥር ዐ58 661 ዐ3 3ዐ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ጨረታውን ያወጣው መሥሪያ ቤትም የተጠየቀውን ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሑፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀናት በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዝግ ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተጠየቀው ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አሸናፊው ከተለየ በኋላ የሚመለስ ለእያንዳንዱ 4,000 (አራት ሽህ ብር) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡