በደቡብ ጎንደር ዞን የእስቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ምድብ 1 ኤሌክትሮኒክስ፣ ምድብ 2 የዉሃ ግንባታ ማቴሪያል፣ ምድብ 3 የመንገድ ጥገናና የማሽን ኪራይ፣ ምድብ 4 የስፖርት ትጥቅ በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚሰሩ ሥራዎችን /የሚገዙ እቃዎችን/ አይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፍል ከግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኝት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና ለኤሌክትሮኒክስ ግዥ 40000 /አርባ ሽህ ብር/፣ ለዉሃግንባታ ማቴሪያል ግዥ 20000 /ሃያ ሽህ ብር/፣ ለመንገድ ጥገና ስራዉ 50000 /ሃምሳ ሽህ ብር/ እና ለስፖርት ትጥቅ ግዥ 5000 /አምስት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሪ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዉል ማሰከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒ.ኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሸጎ 4፡00 ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጎልም፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ቢሆን በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ልዩነት ቢፈጠር በነጠላ ዋጋዉ የሚወሰድ ይሆናል፡፡ የመጫረቻ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለበት ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው በእያንዳንዱ ምድብ በጥቅል ድምር ስለሚወዳደር ሁሉንም እቃዎች መሙላት ይጠበቅበታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 20 67 19 18 /09 18 30 30 12 በመደውል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የእስቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት