ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
77

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፖሊስ ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ሎት 1 ለኮሚሽኑ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል መኪና መለዋወጫ እና ሎት 2 የተለያዩ መጠን ያላቸው የህትመት ሥራዎችን በነጠላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረበዉ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የሚነበቡ /በደንብ የሚታይ/ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. በጥቃቅን እና አነስተኛ የሚወዳደሩ የንግድ ፈቃዳቸው አምስት ዓመት ያልሞላው ለመሆኑ ከቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ አለባችው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ላይ የሚገለጸውን ዋጋ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 128 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን በሎጀ/ፋይ/አስ/ም/ዘርፍ ወይም ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚውል ሲሆን በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በእለቱ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 21 11 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0582201453 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here