ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
109

በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ የፋርጣ ወረዳ ፍ/ቤት የሚገለገልባቸው ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 4 የህትመት ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ  ተጫራቾች መወዳደር  ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  4. የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 20 /ሀያ ብር/ በመክፈል በመ/ቤታችን ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ከዋና ገ/ያዥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት  እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባችሁ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ኦርጅናል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋ/ን/አ/ስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  እስከ 16ኛው ቀን 2፡59 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 3፡00 ሲሆን  የጨረታ ሣጥኑ ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይታሸጋል፡፡
  8. ጨረታዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በ16ኛዉ ቀን 3፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዚጊያና መክፈቻ በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራች በጨረታዉ አሸናፊ ከሆናችሁ በኋላ የምታቀርቡት ደረሰኝ የድርጅቱ ስም፣ ስማችሁ እና የንግድ ፈቃድ አይነት በህትመት የተዘጋጀዉ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ በጨረታ ከሚገዛዉ እቃ መጠን ሃያ በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል፡፡
  11. ማንኛዉም ተጫራች እቃዉን በሎት /በጥቅል/ የሚፈፀም መሆኑ ታዉቆ በእያንዳንዱ ዝርዝር እቃዎች መሙላት ይኖርበታል፡፡ የተዘረዘሩት እቃዎች በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ይደረጋል፡፡
  12. ማንኛዉም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  13. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የሞላዉን ጠቅላላ ዋጋ ቫቱን ጨምሮ አስር በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በማስያዝ ዉል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
  14. የንብረት ርክክቡ የሚፈፀመዉ ፋርጣ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የማጓጓዣ ወጭን እና የጉልበት ወጭን በተመለከተ አሸናፊ ድርጅቱ ይሸፍናል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 24 46/ ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፋርጣ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here