ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
124

የባሕር ዳር ከተማ የአካባቢ ጥበቃ፣ ፅዳትና ውበት ጽ/ቤት በ2016 በበጀት ዓመት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ሁለት ፓርኮች የማስተዳደርና የገቢ ክራይን ሥራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 1ኛ፡- ለዘንባባ መናፈሻ ዝርዝር የጨረታ መስፈርቶች፡-

የቦታው መገኛ ፋሲሎ ክ/ከተማ ቀበሌ 03

  1. የቦታው ልዩ መጠሪያ በቀድሞው ህዳር 11 በአሁኑ ዘንባባ መናፈሻ
  2. የቦታ ስፋት 2.1 ሄክታር
  3. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ በገፀ ምድር ማስዋብ ወይም በካፌ /ሬስቶራንት/ ሆቴል ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  4. የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
  5. የጨረታው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. በመናፈሻው ውስጥ የሚገኙ የገቢ ማስገኛ ምንጮች፡- አንድ የአሳ ካፊና ሬስቶራንት /Fish Corner/፣ አራት ሸድ ያላቸው የቡና መሸጫ /Coffee Corner/፣ አራት የመጽሃፍ ማስቀመጫ ቦታዎች /Book Corner/፣ ለፎቶ፣ ለሰረግ፣ ለምርቃን እና የተለያዩ ዝግጅቶች የሚካሄዱበት መድረክ ያለው፣ ጌጠኛ መቀመጫ ወንበሮች፣ አንድ ፋውንቴን፣ የተለያዩ ለመዝናኛ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን የሚያስተዳድርና ግቢውን የሚከራይ፡፡
  7. የአንድ ሰው የመግቢያ ዋጋ ከ10.00 /አስር ብር/ ያልበለጠ የሚያስከፍል፡፡
  8. በመናፈሻው ውስጥ 100 /አንድ መቶ/ ጌጠኛ ወንበሮች፣ 50 /ሀምሳ/ የውሃ ማጠጫ ስፒሪንግኪለር፣ 8 /ስምንት/ ጌት ቫልቭ፣ 50 አጭር እና 17 /አስራ ሰባት/ ረዥም የመብራት እንዲሁም 10 /አስር/ የመንገድ ዳር መብራት ቢበላሹ እና ጉዳት ቢደርስባቸው ማሠራት የሚችሉ፡፡
  9. የተተከሉ ችግኞች እና ዘመናዊ የሆኑ ኩኩየ ሳር በየጊዜው ውሃ በማጠጣት በማረምና በመኮትኮት አጠቃላይ እንክብካቤ ማድረግ የሚችል በጎደሉት የሚተካ፣ ያለውን በተሻለ ሁኔታ የሚያስቀጥልና የሚያስውብ፣
  10. የውሃ ማጠጫ ፖምፕ ብልሽት ሲገጥም ማሠራት የሚችሉ፡፡
  11. ካሁን በፊት ፓርክ የአስተዳደረ ወይም ያለማ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል እና በሙያው ልምድ ያለው ከሌለውም ልምድ ያለው ባለሙያ መቅጠር የሚችል፡፡
  12. አረንጓዴ ቦታ ለማልማቱ ከሚመለከተው ተቋም የመልካም ሥራ አፈፃፀም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
  13. የሥራ ጊዜዉ ሁለት ዓመት የሚቆይ ሁኖ በየስድስት ወሩ የሚታደስ፡፡
  14. የጨረታ መነሻ ዋጋ 70,000.00 /ሰባ ሽህ ብር/፡፡
  15. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁጥር 1-16 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  16. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ ነጥብ ስድስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  17. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ ነው፡፡
  18. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ ተለይቶ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/ አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 205 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ከ2፡30 እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  19. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 205 በ15ኛው ቀን በ11፡00 ታሽጎ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዛወራል፡፡
  20. በጨረታው ሁለት የግምገማ ሂደቶች ይኖሩታል፡፡ የመጀመሪያው ሂደት /ደረጃ የቴክኒካል ሰነዶች ግምገማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቴክኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች ውስጥ ከፍተኛ ብር ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች መምረጥ ይሆናል፡፡
  21. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 205 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 16 93 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  22. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች የማይመለስ 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቸላል፡፡
  23. መስፈርቱን ያሟላና ከፍተኛ የብር መጠን ያሥገባ አሸናፊ ተጫራች ይሆናል፡፡
  24. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የባሕር ዳር ከተማ የአካባቢ ጥበቃ፣ ፅዳትና ውበት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here