የዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተለያዩ የእድሳት ስራ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ማንኛውንም የሚጠየቁትን መረጃ ማሟላት የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው 200‚000 /ሁለት መቶ ሽህ/ብርና ከዚያ በላይ ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ 100.00 / አንድ መቶ / ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- በ16 ኛው ቀን ኦርጅናሉን በማስገባት ከጧቱ 4፡30 ላይ የጨረታ ሰነዱ ታሽጎ በዚሁ እለት 5፡00 ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚሞሉውት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረብ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ተቋራጮች ደረጃቸው ከደረጃ ከ7-GC/BC እና በላይ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ሲገለጽ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ ሲፒዩ በማስያዝ ውል መፈጸም ይኖርባቸል፡፡ ስራው ከተጠናቀቀ እና ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀን ፀንቶ ይቆያል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 092 047 88 84 ይደውሉ፡፡
የዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል