ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
92

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በኮሌጁ ግቢ ውስጥ ጥልቅ ጉድጓድ ውሃ ለማስቆፈር የውሃ ስራ ተቋራጮችን ሁሉ ከደረጃ 10 እና በላይ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወደድሮ ለማስቆፈር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠየቁትን ግዴታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የተሰጣቸዉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ አቅራቢዎች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የቫት ተመዝጋቢ መሆንዎን የሚገልጽ ማስረጃ እና እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ባዘጋጀው የጨረታ መመሪያና ስፔስፊኬሽን መሰረት መስራት የሚችሉ፡፡
  5. አሸናፊው ተጫራች የሚመረጠው ባቀረበው ጠቅላላ ዝቅተኛ ሎት /ጥቅል/ ዋጋ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የሁሉንም የውሃ ቁፋሮ ሥራ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 14/07/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ ቅፅ ሞልተው ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር የጨረታ ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን /ቢድ ቦንድ/ የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የምታሲይዙ ከሆነ በኮሌጁ ገቢ ደረሰኝ ገቢ አድርጋችሁ የደረሰኙን ኮፒ ከሰነዳችሁ ጋር አያይዛችሁ፤ አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ከቀን 24/06/2017 ዓ.ም እስከ 15/07/2017 ዓ.ም 3፡30 ድረስ እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 01 ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግንባታዎች ላይ ተሳትፈው በውለታችው መሰረት ባለመፈፀማቸዉ ምክንያት ስልጣን ባለው አካል እገዳ ያልተደረገባችሁ መሆን አለበት፡፡
  8. አሸነፊ የሆነ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
  9. እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች የውሃ ቁፋሮ ሥራ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ተሸጦ በ22ኛው ቀን 15/07/2017 ዓ.ም 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 3፡35 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በመክፈቻዉ ዕለት ባይገኙም ጨረታዉ በሰዓቱ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈፃፀም መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ ይሆናሉ፡፡

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here