በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ዋና ጽ/ቤት ለፎገራ ወረዳ ውሃና ኢነርጅ ጽ/ቤት ሎት 1 አፍሬዲየም ፓምፕ ለፎገራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሎት 2 ኤክስካቫተር ከነነዳጁ ኪራይ እና ሎት 3 ቀያማ አፈር ገረገንቲ በድጋሜ የወጣ የተገለጹትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ መወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለምዝገባ በሚመጡበት ወቅት
- በዘርፋ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ካርድ ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት በፎ/ወ/ገ/ኢ/ል/ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 150 /አንድ መቶ አምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላትና በደንብ ፖስታውን በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር በማድረግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጽ/ቤታችን ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ለሎት 1 ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ ሎት 2 ብር 140,000 /አንድ መቶ አርባ ሽህ ብር ሎት 3 ብር 20,000 /ሀያ ሽህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- ሰነዱን ለሚገዙ ተጫራቾች ዝርዝርና /ስፔስፊኬሽን/ ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ድርጅት ውል እንደያዘ ጨረታ ላላሸነፋት አካላት ተመላሽ ይሆናል፡፡
- አንድ ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- አሸናፊው በውሉ መሠረት ከላስረከበ መ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን መረዳት ይኖርበታል፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ ተደረጅተው ለሚመጡ አካላት ካደራጃቸው ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
- ኤክስካቫተሩ የፈረስ ጉልበቱ 320 HP የሆነ የአካፋ መጠን 1.5 ሜ/ኩ መሸከም የሚችል ማሽን ለ672 ሰዓት የሥራ ቦታው ጉማራ ወንዝ ርብ ወንዝና ጓንታ ወንዝ ሲሆን ገረገንቲው የሚቀርበው ርብና ጉማራ ነው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል ከመፈራራሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አሰፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአሸናፊ ተጫራች የቀረበው በወድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ ሃያ በመቶ መቀነስ ወይም መጨመር የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 446 20 26 በመደወል ጠይቀው መረዳት ይችላሉ፡፡
- ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የፎገራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት