የማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሥራ ሂደቶችና ለምድብ ችሎቱ አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎችን ለመግዛት ሎት 01 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 03 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 04 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 05 የፈርኒቸር እቃዎች በሎት ለመግዛት መስፈርቱን አሟልቶዉ ከሚገኙ አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሥለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የታደሰ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት አያይዘዉ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ግዥዉ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ለሚፈጸሙ ግዥዎች እና ለኤሌክትሮኒክስ ነክ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ከማ/ጎን/ከፍ/ፍ/ቤት የግ/ፋ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም በጋዜጣ ተለጥፎ ቆይቶ መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በታሸገበት ቀን ከቀኑ 8፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጨረታዉ ማ/ጎ/ዞን/ከ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በቀኑና በሰዓቱ ካልተገኙ ጨረታዉን ከመክፈት አያግድም፡፡
- የዕቃ ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ሙሉዉን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት ድምር ከሞሉት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከመ/ቤታችን የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ከገንዘብ ያዥ በመ/ሂ1 ደረሰኝ አስቆርጦ ከሚወዳደርበት ሰነድ ጋር የደረሠኝ ኮፒ በማሸግ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ዋና ሠነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸዉ ቦታ መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ሰነዱን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የእቃዉን መጓጓዣና እንዲሁም ማንኛዉንም የመንግስት ታክስን ያካተተ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ዉድድሩ በሎት ድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ካለዎት ግዥና ፍይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 111 44 40 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት