ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
141

የባሕር ዳር ከተማ የአካባቢ ጥበቃ፣ ፅዳትና ውበት ጽ/ቤት በ2016 በበጀት ዓመት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ሁለት ፓርኮች የማስተዳደርና የገቢ ክራይ ሥራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 1ኛ፡- የአሮጌው ዲፖ/ጣና መናፈሻ ዝርዝር የጨረታ መስፈርቶች፡-

  1. የቦታው መገኛ ጣና ክ/ከተማ ሽንብጥ ቀበሌ፡፡
  2. የቦታው ልዩ መጠሪያ በቀድሞው አሮጌው ዲፖ በአሁኑ ጣና መናፈሻ፡፡
  3. የቦታው ስፋት 4.7 ሄክታር
  4. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ በገፀ ምድር ማስዋብ ወይም በካፌ/ሬስቶራንት /ሆቴል ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  5. ግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
  6. የጨረታው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. በመናፈሻው ውስጥ የሚገኙ የገቢ ማስገኛ ምንጮች፡- አንድ ካፊና ሪሰቶራንት፣ የትኬት መቁረጫ ክፍሎች ያሉት፣ የስፖርት ማካሄጃ፡- አንድ የእግር ኳስ /ለመጫዎቻ የማይውል/፣ አንድ የመረብ ኳስ፣ አንድ የእጅ ኳስ፣ ሁለት የቅርጫት ኳስ፣ ሁለት የአሽዋ ላይ ጭዋታ ቦታዎች፣ አንድ የሜዳ ቴንስ መጫዎቻ፣ ለፎቶ፣ ለሰረግ፣ ለምርቃን እና ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚካሄዱበት መድረክ ያለው፣ የማይንቀሳቀሱ ጌጠኛ መቀመጫ ወንበሮች እና የተለያዩ ለመዝናኛ አገልግሎት የሚዉሉ ቦታዎችን በአግባቡ የሚያስተዳድርና ገቢውን የሚከራይ፣
  8. የአንድ ሰው የመግቢያ ዋጋ ከ10.00 /አስር ብር/ ያልበለጠ የሚያስከፍል፡፡
  9. በመናፈሻዉ ውስጥ 164 /አንድ መቶ ስልሳ አራት/ ጌጠኛ ወንበሮች፣ የውሃ ማጠጫ መስመሮች፣ 20 /ሃያ/ የመንገድ መብራት፣ 4 /አራት/ ትልልቅ የባውዛ መብራት፣ 30 /ሰላሳ/ መካከለኛ የባውዛ መብራትና 290 /ሁለት መቶ ዘጠና/ ትንንሽ የባውዛ መብራት ቢበላሹ እና ጉዳት ቢደርስባቸው ማሠራት የሚችል፡፡
  10. የተተከሉ ችግኞች እና ዘመናዊ የሆኑ ኩኩየ ሳር በየጊዜው ውሃ በማጠጣት በማረምና በመኮትኮት አጠቃላይ እንክብካቤ ማድረግ የሚችል በጎደሉት የሚተካ፣ ያለውን በተሻለ ሁኔታ የሚያስቀጥልና የሚያስውብ፡፡
  11. የውሃ ማጠጫ ፖምፕ ብልሽት ሲገጥም ማሠራት የሚችል፡፡
  12. ካሁን በፊት ፓርክ የአስተዳደረ ወይም ያለማ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል እና በሙያው ልምድ ያለው ከሌለውም ልምድ ያለው ባለሙያ መቅጠር የሚችል፡፡
  13. አረንጓዴ ቦታ ለማልማቱ ከሚመለከተው ተቋም የመልካም ሥራ አፈፃፀም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
  14. የሥራ ጊዜው ሁለት ዓመት የሚቆይ ሁኖ በየ ስድስት ወሩ የሚታደስ፡፡
  15. የጨረታ መነሻ ዋጋ 100,000 /አንድ መቶ ሽህ ብር/፡፡
  16. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-16 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  17. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የአቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ ነጥብ ስድስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  18. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ ነው፡፡
  19. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ ተለይቶ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/ አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 205 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ2፡30 እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  20. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ/ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 205 በ15ኛው ቀን በ11፡00 ታሽጎ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዛወራል፡፡
  21. በጨረታው ሁለት የግምገማ ሂደቶች ይኖሩታል፡፡ የመጀመሪያው ሂደት/ደረጃ የቴክኒካል ሰነዶች ግምገማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቴክኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች ውስጥ ከፍተኛ ብር ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች መምረጥ ይሆናል፡፡
  22. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 205 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 16 93 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  23. የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች የማይመለስ 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
  24. መስፈርቱን ያሟላና ከፍተኛ የብር መጠን ያስገባ አሸናፊ ተጫራች ይሆናል፡፡
  25. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የባሕር ዳር ከተማ የአካባቢ ጥበቃ፣ ፅዳትና ዉበት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here