የባ/ዳር ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል Invertor with Battery, product Description 5KW—5KVA 48V Hybrid invertor በሚሰጠዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆኑም፡-
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርቶች /ማስረጃዎች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባ/ዳር ጤ/ጣ ቢሮ ቁ 06 በመምጣት የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉትን የጨረታ ሰነድ አንድ ዋና እና ኮፒ እንዲሁም የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ዋስትና በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ ብር በሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ የተጠቀሰውን /መስፈርቶች ወይም ማስረጃዎች ማሟላት የምትችሉ ተጋባዦች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከ01/07/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ባ/ዳር ጣቢያ መምጣት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
- ጨረታውን የሚከፈተው በ15ኛው ቀን ማለትም በ15/07/2017 ዓ.ም ከቀኑ በ11፡30 ተዘግቶ በቀጣይ ቀን በ 16/07/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስትሞሉ ሥርዝ ድልዝ መሆነ የለበትም አሸናፊው ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በአምስት ቀን ውስጥ እቃውን ተቋሙ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ቢሮ ቁጥር 06 ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 0043 /058 220 34 20/058 220 49 40 መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡
የባህር ዳር ጤና ጣቢያ