የጨረታ ቁጥር፡- 01/2017
በምሥራቅ ጎጃም ዞን የደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ማለትም የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ብትን ጨርቅ፣ ህትመቶች፣ የውሃ እቃዎች እና የሞተር ዘይት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 50 /ሃምሳ ብር/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ ሰነድ በመግዛት ደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 85 መዉስድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የተጠየቁትን ዕቃዎች በተሰጠዉ ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሙላት ያለባቸዉ ሲሆን፣ ናሙና ለሚያስፈልጋቸዉ የተለያዩ እቃዎች ሆስፒታሉ በሚያቀርበዉ ናሙና መሰረት የሚቀርብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ፣ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያዉ ላይ በመፈረም ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ እስከ 16ኛዉ ቀን እስከ ጠዋት 3፡30 ድረስ በሆስፒታሉ ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 85 በሚገኘዉ ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ ጨረታዉ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታዉን ይከፍታል፡፡ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻለዉ እስከ 15ኛዉ ቀን 11፡30 ድረስ ብቻ ነዉ፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ዝግ ወይም በዓል የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታዉን በሎት ወይም ጠቅላላ ዋጋ የሚያወዳድር ሲሆን በአንድ ምድብ ዉስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ዉስጥ ሳይሞሉ መተዉ አይቻልም፡፡ በሎት ያልሞላ ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸዉን ዕቃዎች ደጀን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸላቸዉ ከ5 ሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርበዉ ዉል መያዝ አለባቸዉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 85 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 776 13 18 መደወል ይቻላል፡፡
የደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል