በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ እና ሎት 3 ሌሎች ቋሚና አላቂ እቃዎች ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሃሳባቸውን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣበት በመጀመሪያ ቀን አንስቶ ተከታታይ 15 ቀናት ቆይቶ የሚውል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት አስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/አስ/ደ/የስራሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በ16ኛው ቀን 4፡15 ላይ ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሠነዱን ቢሮ ቁጥር 7 ብር 50 (ሀምሳ ብር) የማይመለስ በመክፈል መውሠድ ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ሰፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 661 00 02 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የሚገዙትን እቃዎች ሃያ በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አሸናፊው ተቋሙ ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በሎቱ ወይም በጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000 ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ማስያዝ አለባቸው፡፡
የሞጣ ከተማ ጤና ጥበቃ ጣቢያ