የአዊ ብሄረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ሜዲካል ኦክስጅን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ውል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መጫረት ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የታደሰ እና በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ እና ሜዲካል ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1 – 3 የተጠቀሱትን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ 3 የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት በልዩ ልዩ ምክንያት በሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ያልታገዱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በዋጋ መሙያው ቅፅ ላይ ማንኛውንም የመንግሥት ግብር ያካተተ ሆኖ የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ የድርጅቱ ክብ ማህተም፣ ፊርማ፣ ስም እና አድራሻ በማስቀመጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ግዥ የሚሞሉትን ጠቅላላ ድምር ማንኛውንም ግብር ጨምሮ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና /ቢድ ቦንድ/ ወይም በሆስፒታሉ የገቢ ደረሰኝ መሂ-1 ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብሮ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከታወቀ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ፕሮግራሙ የማይስተጓጎል ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች እቃውን በራሳቸው ወጪ እስከ ሆስፒታሉ ድረስ በማምጣት ገቢ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በ058 827 04 27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡