የግዥ መለያ ቁጥር አ/ማ/03/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ኮሚሽን በጦርነቱ ለተጎዱ የመንግስት ተቋማት እና ለዲጅታል አይዜሽን አገልግሎሉ የሚዉል የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች ማለትም እንደ ኮምፒተር ፡ ፕሪንተር ፡እስካነር እና የመሳሰሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይበተ.ቁ. 1- 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እቃዎች የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት መግዛትይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በ16ኛዉ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ግምገማ ለሚያስፈልጋቸዉ ዕቃዎች የመጫረጫቻ ሰነዱን በትክክል ከሞሉ በኋላ ቴክኒካሉን እና ፋይናሻሉን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን እና ሰአት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉበሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582220580 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0582209644/0582209646 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ኮሚሽን