ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
96

የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ለ2017 በጀት አመት በመደበኛ በጀት፣ በፌደራል ድጐማ በጀት እና ከገቢ ማሰባሰቢያ በተገኘ በጀት 1ኛ. ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ ፣2ኛ. ሎት2. ህትመት  ፣3ኛ. ሎት 3.  ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማች ዕቃዎች ፣4ኛ. ሎት 4. የጽዳት ዕቃዎች ፣ 5ኛ. ሎት 5 የመኪና ዲኮር /ጌጣጌጥ/፣ 6ኛ. ሎት 6. የመኪና ጎማ ከነካላማዳሪው፣ 7ኛ. ሎት 7. የብስከሌት ጎማ ከነካላማዳሪው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው ። ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት በባህርዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በቢሮው ቢሮ ቁጥር 11 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከመጋቢት 08 ቀን 2017 እስከ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባህርዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0908649967 በመደወል ማግኘት ይችላል፡፡

የአብክመ  ጠቅላይ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here