ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
85

በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በUNDP በጀት ለጃናሞራ ወ/ት/ት ጽ/ቤት ለተማሪዎች ለመማሪያና ማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ ሎት1.ኮንባይን ዲስክ የተማሪዎች ወንበር፣ ሎት2.ጥቁር ሰሌዳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ  ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው ፡፡
  2. የቲን ነምበር ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው ፡፡
  3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርቲፊኬት ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከ1–4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በእያንዳንዱ ሎት የዕቃወቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1.5 በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ጀምሮ በአየር ላይ ከ 08/07/2017 ዓ/ም እስከ 22/07/2017 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከ08/07/2017 እስከ-22/07/2017 ድርስ ማስገባት ይቻላል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 23/07/2017 ዓ/ም 8፡15  ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታውን ከመክፈት  አያስተጓጉለውም፡፡
  11. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
  13. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው ፡፡
  16. ተጫራቾች የእቃዎቹን ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ-ብርሃን ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው የሚያስረክቡ ሲሆን ትራስፖርትን እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ. 0582940023/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
    የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here