ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

የአብክመ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የተለየዩ የመኪና ዘይት እና ቅባት ፣ የጽዳት እቃ፣ የፕሪንተር ቀለም፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና መለዋወጫ እቃ ፣ ፕላስቲክ ማዳበሪያ ግዥ ፤እንዲሁም የብስክሌት ጥገና የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢነት ሰርቲፊኬት እና የሚገዙ እቃዎች ዋጋ ከ200 ሽህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርቲፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 እስከ 3 የተገለጹትን መስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የሚገዙ የመኪና ዘይት እና ቅባት ፤የጽዳት እቃ፣ የፕሪንተር ቀለም፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና መለዋወጫ እቃ ፣ ፕላስቲክ ማዳበሪያ ግዥ የብስክሌት ጥገና አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃ / የአገልግሎት/ ግዥ የጠቅላላ ዋጋውን 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ.) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት፡፡
  9. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳር የሚቀጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና  ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በአል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ጨረታዉ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 0582180014/ 0582181103 ይደውሉ፡፡

አ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን

  ባህር ዳር

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here