ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
96

አብክመ/ውኢቢ/ግጨ/ዕግ/ቁጥር-002/2017

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውኃና ኢነርጅ ቢሮ ከአማራ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት በሚያገኘው የበጀት ድጋፍ ሎት 1. የሶላርዕቃዎች የዕቃ አቅርቦት ግዥና ሎት 2. የጠላቂ ፓምፕ የዕቃ አቅርቦት ግዥ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ዕቃውን /አገልግሎቶችን ለማቅረብ በዘርፉ (የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች  አቅራቢነት) ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ  ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሀና ኢነርጅ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሽህ ብር/ ብቻ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃና ኢነርጅ፣ ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 27 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ለሎት 1 ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/፣ ለሎት 2 ብር 300,000 /ሦስት መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማቅረብ  አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 8/7/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው መዝጊያ ቀን ደግሞ 24/7/2017 ዓ.ም መሆኑን  እየገለፅን  በዚሁ ቀን 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የሥራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ /ቅጽ/ መሰረት መሙላት ይኖርበታል፡፡
  9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251 582 26 24 60 /+251 582 20 08 55 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአብክመ ውሃና ኢነርጅ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here