የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት 1ኛ/የመ/ቤቱ ህንፃ ፊት ለፊቱ የቀለም ቅብ እና ሌሎች ጥገናዎችን ለማሰራት ስለተፈለገ ከደረጃ 5 እና በላይ የሆኑ ህንፃ ተቋራጮችን እና 2ኛ የጽሕፈት መሳሪያ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- ማንኛዉም ተጫራች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ለዚህ የተዘጋጀውን ሠነድ ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመቅረብ በ100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
- የጨረታው ሠነድ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ መሞላት ይኖርበታል፡፡
- የተሞላው ዋጋ ቫትን የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ መግለጽ ይኖርበታል፡፡ የተገለፀ ነገር ከሌለው ከቫት ጋር እንደተሞላ ይቆጠራል፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዛቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ከሠነድ ጋር አብሮ አያይዞ መቅረብ አለባቸው፡፡
- የቀለም ቅብ እና ሌሎች ጥገናዎችን ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ለጽሕፈት መሳሪያ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ ቁጥር 013 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 27 19 /058 220 52 69 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት