ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
125

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ 1. የህሙማን ምግብ አቅርቦት፣ 2. የልብስ እጥበት አገልግሎት፣ 3. አትክልት ማስዋብና የጉልብት ሥራ አገልግልት፣ 4. የጥበቃ አገልግሎት እና 5. የፅዳት አገልግሎቶችን በማህበር ለተደራጁ ወይም ሕጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅቶች እና ማህበራት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፡-

  1. ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላችሁ እና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፡፡
  2. ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባችው፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች ያሸነፉበት የሥራ ዋጋ ድምር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ሁለት በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ መሥሪያ ቤቱ ቫት ይሰበስባል፡፡
  6. ግዥ ፈፃሚው መሥሪ ቤት በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት ሥራዎች ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  7. ተጫራቾች የሞሉትን የሥራ ዋጋ፣ አንድ በመቶ በጨረታ ማስክበሪያ ቢድ ቦንድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በማሲያዝ ከፖስታው ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
  9. ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራችው በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  11. ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን ግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-5 ያሉትን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ10/10/2016 ዓ.ም እስከ 30/10/2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ለ21 ቀናት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  13. የጨረታ ሳጥኑ በ30/10/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፡፡
  15. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በሥራ ሂደቱ ስልክ ቁጥር 033 331 02 52 ደወሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  17. የጨረታ መክፍቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  18. አሽናፊው የሚለየው በሎት ድምር ነው፡፡
  19. አሸናፊው ማሸነፉ ተነግሮት ውል ከወሰደ በኋላ ሆስፒታሉ በሚያዘው መጠን ማቅረብ አለበት፡፡
  20. አሸናፊው ድርጅት ውለታ ከወስደበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/10/2017 ዓ.ም ድረስ ሆስፒታሉ ሥራ ብሎ ሲያዘው በታዘዘው መሰረት መሥራት አለበት፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • የህሙማን ምግብ አቅርቦት እና የልብስ እጥበት ሥራዎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን እና መብራት እና የውሃ አገልግሎት ወጭዎች በአሽናፊ ተጫራቾች የሚሸፈኑ ይሆናል፡፡
  • የአትክልት ማስዋብና የጉልበት ሥራ አገልግሎት፤ የጥበቃ አገልግሎት እና የፅዳት አገልግሎት የሰው ሃይል ቁጥር እና የደንብ ልብስ አይነት የሚወሰነው እንደሥራው ስፋት እየታየ በሆስፒታሉ የሥራ አመራር ኮሚቴ የሚወሰን ይሆናል፡፡

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here