ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
125

የጎንደር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማእከል ለማዕከሉ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ሎት 5 የፎቶ ኮፒና የኤሌክትሮኒክስ  ጥገና እና ሎት 6 የፈርኒቸር ጥገና   በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው፡-

  1. በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዋጋውን አንድ በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ማዘዣ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታውን ሰነድ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ገንዘብ ቤት የማይመለስ ብር 50 /አምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ጨረታው ከ08/07/17 እስከ 22/07/2017 ዓ.ም ለተከታታይ ቀን በጋዜጣ የሚቆይ ሲሆን በ 23/07/2017 ዓ.ም ከቀኑ በ4፡00 ጨረታው ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ግዥና ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቹ በሌላ ሰው ዋጋ ተንተርሶ ወጋ መስጠት አይችልም
  9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በማዕከሉ በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 211 74 87 ወይም 0918 03 15 30 /0918 03 23 67 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  10. አድራሻችን ጎንደር ቀበሌ 18 ከፍሎሪዳ ሆቴል ፊት ለፊት ወደ መስጊድ በሚወስደዉ መንገድ ከአቶ አብይ ምትኩ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ነው፡፡
  11. ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጎንደር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማእከል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here