ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
92

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ኃ.የተወሰነ ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን መነሻውን ደብረ ታቦር ከተማ በማድረግ 35,000 ኩንታል በላይ የተለያዩ የሰብል ምርጥ ዘር በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ዞኖችና ከክልሉ ውጭ ባሉ ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ተጓጉዞ እንዲሰራጨለት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በትራንስፖርት አገልግሎት ውድድር ላይ የምትሳተፉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡ ማለትም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የንግድ ፈቃድ ቲን ነብር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የመኪና ሊብሪ /ስመ-ንብረት/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከታወቀ ባንክ /በጥሬው/ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. የሰነድ መግዣ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጉና የዘር ብዜትና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኔዬን በሚገኝበት ደብረ ታቦር ከተማ ቀበሌ 02 ደሴት ላይ ቡና ባንክ ፒተር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
  6. ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ በጥንቃቄ በማሸግ የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በቀን 16/07/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ ጉና የዘር ብዜትና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን ደብረ ታቦር ከተማ ፒተር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03 ላይ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ሳይገኙ ቢቀሩ እንደተገኙ ተቆጥሮ የጨረታ ፖስታው እንዲከፈት ተደርጎ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን /ካላንደር/ ቢሆን ወደ ሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዛወራል፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ተለጥፎ የሚቀይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከመጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ/ም ጀመሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ብቻ ይሆናል፡፡
  10. ሙሉ መረጃውን ከሰነዱ ያገኛሉ ለበለጠ መረጃ 09 30 70 99 26 /09 79 26 13 56 /09 18 21 87 40
  11. ዩኔኑ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የሚሰራጨው የሰብል ምርጥ ዘር መጠን ሊቀንስ /ሊጨምር/ ይችላል፡፡
  13. ዩኔኑ አሸናፊውን የሚለየው በዝቅተኛ ነጠላ ዋጋ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የተጠየቁትን ዝርዝር ዋጋ ለማወዳደር ያመች ዘንድ አካተው መሙላት አለባቸው ይህም በዩኔኑ ግዥንና ሽያጭ መመሪያ መሰረት የሚፈፀም የሆናል፡፡

ጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here