ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
96

በአብክመ ክልል ም/ቤት በ2017 በጀት ለኮድ 4-03998፣ 4-06956፣ 4-02312 የመኪና እቃ እና ኮድ 4-3823 ሞተር እቃዎች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. በዘርፉ ታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው።
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200.000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨራቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ዝርዝር መግለጫውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ / በመክፈል ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ ፡፡
  7. ሰነዱን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት /15  /መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ መስከበሪያ /ቢድ ቦንድ /1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ /ሲፒኦ /በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መስያዝ የሚፈልጉ ለጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመክፈል ደረሰኙን ከዋጋ መቅረቢያው ጋር ማቅረብ የኖርባቸዋል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በተሸገ ፖስታ በክልል ምክር ቤት ፅ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀው የጫረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ16ኛው ቀን እስከ ጥዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ቢሮ ቁጥር 40 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል ፡፡ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም  በከፊል  የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡
  11. ዝርዝር የእቃው አይነት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አማራ ክልል ምክር ቤት ቢሮ ቁጥር 40 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582262151 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ማንኛውም ለስራው የሚያስፈልጉ ወጭዎች በአሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል። ከነዚህ በተጨማሪ የግዠ መመሪያ 1/2003 ተግባራዊ ይደረጋል።

የአብክመ ምክር ቤት /ጽቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here