የደቡብ ጐንደር አስተዳደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 2 የወለል ምንጣፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በሎት ከጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ አንድ መቶ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ደ/ጐን/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 በመቅረብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በፖስታ ውስጥ አሽጐ ማቅረብ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፣ ገንዘቡም ቢጠፋ መ/ቤቱ ሊጠየቅ አይችልም፡፡
- መ/ቤቱ ለመግዛት የሚፈልገውን እቃዎች አይነት ዝርዝር የያዘ ሠነድ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 35 በመምጣት እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 35 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ተወካዩች ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛዉ ቀን 2፡30 ቢሮ ቁጥር 35 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠዉ ወይም የሚለዩት በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ ነዉ፡፡
- አሽናፊው ድርጅት የአሸናፈዉን እቃ ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ኦሪጅናል እና ኮፒ ፈቃድ በመያዝ ሰነዱን በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸዉ አማካኝነት ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 03 86 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ጐንደር አስተዳደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት