ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ ለ2017 ዓ.ም የተጠቃለሉ ህጎች ቅጽ 4 ህትመት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የተጠቃለሉ ህጎች ቅጽ 4 ህትመት በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው ነገር ግን ከላይ ከ1-2 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል አብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 /ከገንዘብ ያዥ ቢሮ/ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን ዋጋ የተጠቃለሉ ህጎች ቅጽ 4 ህትመት 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ማህተማቸውንና ፊርማችን በማሰፈርና ፖስታውን በሚገባ በማሸግ ለአብክመ ፍትህ ቢሮ ግዥ ባለሙያዎች ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ 15/07/2017 እስከ 30/07/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አብክመ ፍትህ ቢሮ ቁጥር 04፣ በ16ተኛው ቀን በ30/07/2017 ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በሚገዙ የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግት ፍትህ ቢሮ
ባህር ዳር